የወልቂጤ ከተማ እና አሰልጣኞቹ ውዝግብ እልባት አግኝቷል

በወልቂጤ ከተማ እና በአሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው እንዲሁም ረዳቱ ኢዮብ ማለ መካከል የነበረው ውዝግብ እልባት አግኝቷል።

የወልቂጤ ከተማ አሰልጣኝ የነበሩት አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው እና ረዳቱ እዮብ ማለ የክለቡ አሰልጣኝ በመሆን እያገለገሉ ባለበት ወቅት ክለቡ ሁለቱንም ከሥራ አግዶ እንደነበር ይታወሳል። አሰልጣኞቹም ለፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ባቀረቡት ቅሬታ መሠረት ለአሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው የአራት ወር ረዳት አሰልጣኝ ለነበሩት እዮብ ማለ ደግሞ የሦስት ወር ደሞዛቸው በሰባት ቀናት ውስጥ ክለቡ እንዲፈፅም ተወስኖ ነበር።

አሁን እንዳገኘነው መረጃ ወልቂጤ ከተማ ዲሲፒሊን ኮሚቴ በወሰነው ውሳኔ መሰረት ለሁለቱም አሰልጣኞች ሙሉ ለሙሉ ከነጥቅማጥቅማቸው ክፍያውን በመፈፀሙ ክሱ መቋረጡን የህግ ጠበቃው ብርሀኑ በጋሻው ነግረውናል።