ኢትዮጵያ ቡና ተጨማሪ ሁለት ተጫዋች አስፈርሟል

በክልል ክለቦች ሻምፒዮና ላይ ጥሩ አቋም ያሳዩት ሁለት ተጫዋቾች ወደ ኢትዮጵያ ቡና አምርተዋል።

በሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው የክልል ክለቦች ዓመታዊ ውድድር ላይ የአሰልጣኝ ተመስገን ዳናን ትኩረት የሳበው እና የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነቱን እየመራ የሚገኘውን አንተነህ ተፈራን ኢትዮጵያ ቡና ማስፈረሙን መዘገባችን ይታወቃል። አሁን ባገኘነው መረጃ መሰረት ደግሞ ከዛው ከሻኪሶ ከተማ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ማስፈረሙን አውቀናል።

አንደኛው ፈራሚ ብርሀኑ ወልቂጦ በመሀል ተከላካይነት የሚጫወት ሲሆን ሌላኛው ፈራሚ የኛነህ ታሪኩ ደግሞ አጥቂ ነው። ተጫዋቾቹ ለምን ያህል ዓመት ከክለቡ ጋር እንደሚቆዩ ግን ይፋ አልተደረግም።