ማሊያዊው ግብ ጠባቂ በፋሲል ከነማ ውሉን አድሷል

ፋሲል ከነማን ላለፉት አራት ዓመታት ያገለገለው ሚኬል ሳማኬ ከክለቡ ጋር መቆየቱ እርግጥ ሆኗል።

የ2014 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን በደረጃ ሰንጠረዡ ሁለተኛ ላይ ተቀምጦ ያገባደደው ፋሲል ከነማ ከአሰልጣኝ ኃይሉ ነጋሽ ይፋዊ ሹመት በፊት አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም እና ውላቸው የተጠናቀቁትን በማራዘም ላይ ይገኛል።

በዛሬው ዕለት ደግሞ ያለፉትን አራት ዓመታት በርካታ ጨዋታዎችን በመሰለፍ ክለቡን በወጥነት ማገልገል የቻለውን ማሊያዊውን ግብ ጠባቂ ሚኬል ሳማኬን ኮንትራት ለሁለት ተጨማሪ የውድድር ዓመታት አድሷል፡፡