ድሬዳዋ ከተማ አማካይ አስፈርሟል

የሦስት ተጫዋቾችን ዝውውር እስካሁን ያገባደደው ድሬዳዋ ከተማ ዮሴፍ ዮሐንስን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

ባሳለፍነው ሳምንት ዮርዳኖስ ዓባይን ዋና አሠልጣኛቸው አድርገው የሾሙት ድሬዳዋ ከተማዎች የግብ ዘቡ ዳንኤል ተሾመ፣ እያሱ ለገሠ እና ኤሊያስ አህመድን ዝውውር ይፋ ያደረጉ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊት ደግሞ ዮሴፍ ዮሐንስን የግላቸው ማድረጋቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

የቀድሞ የሲዳማ ቡና ተጫዋች ከአዳማ ከተማ ጋር ከተለያየ በኋላ ጉዞውን ወደ ምስራቁ የሀገራችን ክፍል ድሬዳዋ አድርጓል።