መከላከያ ራሱን ማጠናከሩን ቀጥሏል

በአሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመራው መከላከያ ስምንተኛ አዲስ ተጫዋች ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

በቀጣዩ ዓመት ስብስቡን አጠናክሮ ለመቅረብ ከአሠልጣኝ ቅጥር ጀምሮ የወሳኝ ተጫዋቾችን ዝውውር እያገባደደ የሚገኘው መከላከያ በዛሬው ዕለት ስምንተኛ አዲስ ተጫዋች ማግኘቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ቡድኑን የተቀላቀለው ተጫዋች አምሳሉ ጥላሁን ነው። የቀድሞ የዳሽን ቢራ ተጫዋች የነበረው የግራ መስመር ተከላካዩ አምሳሉ ያለፉትን ስድስት ዓመታት በፋሲል ከነማ ያሳለፈ ሲሆን ዓምናም የሊጉን ዋንጫ ከፍ ማድረግ ችሎ ነበር። ተጫዋቹም ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ በሁለት ዓመት ውል መዳረሻው መከላከያ ሆኗል።

ጦሩ ከዚህ ቀደም ተስፋዬ አለባቸው፣ በረከት ደስታ፣ ከነዓን ማርክነህ፣ ፍፁም ዓለሙ፣ ሳሙኤል ሳሊሶ፣ ዳግም ተፈራ እና ምንይሉ ወንድሙን ማስፈረሙ ይታወቃል።