ድሬዳዋ ከተማ ተጨማሪ ተጫዋች አስፈርሟል

በአሠልጣኝ ዮርዳኖስ አባይ የሚመራው ድሬዳዋ ከተማ የመስመር ተጫዋች ወደ ስብስቡ ሲቀላቅል የሁለት ተጫዋቾችንም ውል አድሷል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በመጨረሻው ሳምንት በሊጉ መክረሙን ያረጋገጠው ድሬዳዋ ከተማ አሠልጣኝ ዮርዳኖስ አባይን በመንበሩ ሾሞ በዝውውር ገበያው እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊትም የመስመር ተጫዋች ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።

ቡድኑን የተቀላቀለው ተጫዋች ያሬድ ታደሠ ነው። ያለፉትን ሁለት ዓመታት በወልቂጤ ከተማ ያሳለፈው ያሬድ በቀድሞ ክለቡ ዳግም ግልጋሎት ለመስጠት የሁለት ዓመት ውል ፈርሟል።

በተያያዘ ዜና ድሬዳዋ ከተማ የተከላካይ እና የተከላካይ አማካይ ቦታ ላይ ዘንድሮ ግልጋሎት ሲሰጥ የነበረውን አቤል አሰበ እንዲሁም የመስመር ተከላካዩን ያሲን ጀማል ውል ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ማደሱ ተገልጿል።