የአምሳሉ ጥላሁን ማረፊያ ታውቋል

ከሰሞኑ አነጋጋሪ የነበረው የግራ መስመር ተከላካዩ ጉዳይ እልባት አግኝቷል።

በክረምቱ ከፍ ባለ ሁኔታ በመንቀሳቀስ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ የሚገኘው መከላከያ ከቀናት በፊት በፋሲል ከነማ መለያ የሚታወቃው አምሳሉ ጥላሁንን በእጁ ማስገባቱ በፎቶ በታጀበ ማስረጃ ይፋ አድርጎ ነበር። ነገር ግን ተጫዋቹ በጦሩ ቤት ሁለት ዓመታትን ይቆያል ተብሎ ሲጠበቅ የቀድሞው ክለቡ ውሉን አራዝሞ እንዲቆይ ለማድረግ ጥረት የመጀመሩ ጉዳይ ባለፉት ቀናት ሲነገር ቆይቷል። ተጫዋቹም ከመከላከያ ጋር የፈፀመው ውል እንዲፈርስለት ጥያቄ ማቅረቡን ትናንት ዘግበን ነበር።

ዛሬ ፋሲል ከነማ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረትም አምሳሉ ጥላሁን ከመከላከያ ጋር ያደረገውን ቅድመ ስምምነት በማፍረስ ለቀጣይ ሁለት የውድድር ዓመታት ከዐፄዎቹ ጋር ለመቀጠል በመስማማት በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በመገኘት ፊርማውን አኑሯል።