ፈረሰኞቹ ወደ ታንዛኒያ ተጉዘው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ኢትዮጵያን የሚወክሉት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከታንዛኒያው ኃያል ክለብ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ እንደሚያደርጉ ታውቋል።

የ2014 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባለድል የሆኑት ፈረሰኞቹ በወርሐ ጳጉሜ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ለሚኖራቸው የማጣርያ ጨዋታ በትናትናው ዕለት የቅድመ ዝግጅት ልምምዳቸውን ቢሸፍቱ በሚገኘው የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ጀምረዋል። ከዝግጅታቸው ጎን ለጎን በቀጣይ ሳምንት ከሐምሌ 28 -30 ባሉት ቀናት ከታንዛንያው ኃያል ክለብ ሲንምባ ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታ ለማድረግ ቀጠሮ የያዙ ሲሆን ጨዋታውንም ታንዛኒያ ላይ እንደሚያደርጉ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

ቡድኑ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሀገራዊ ግዳጅ ላይ ከሚገኙት ተጫዋቾች በቀር በውጭ የሚገኙትን ተጫዋቾች ጨምሮ አብዛኛው አባላት ወደ አግኝቶ ዝግጅቱን እየሰራ እንደሆነ አውቀናል።