አዳማ ከተማ ከግብ ጠባቂው ጋር በስምምነት ተለያይቷል

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን አዳማ ከተማን ያገለገለው የግብ ዘቡ ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል።

አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ የሾመው አዳማ ከተማ በስፋት ወደ ዝውውሩ ገቢያ እየገባ ባይገኝም አሁን ከግብ ጠባቂው ጀማል ጣሰው ጋር መለያየቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ረጅም ጊዜ በቋሚነት ያገለገለው ጀማል ጣሰው
ሀዋሳ ከተማ፣ ደደቢት፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ መከላከያ፣ ጅማ አባ ቡና፣ ድሬዳዋ ከተማ፣ ፋሲል ከነማ እና ወልቂጤ ከተማ ተጉዞ የተጫወተ ሲሆን ባለንበት ዓመት ደግሞ በአዳማ ከተማ ቆይታ ካደረገ በኋላ የአንድ ዓመት ቀሪ ኮንትራት እየቀረው በዛሬው ዕለት ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል።