ወልቂጤ ከተማ አማካይ አስፈርሟል

ወደ ዝውውሩ ዘግየት ብሎ ቢገባም በርከት ያሉ አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረም የቻለው ወልቂጤ ከተማ ተጨማሪ ተጫዋች የግሉ አድርጓል፡፡

ከአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ ሹመት ቀደም ብሎ ወደ ዝውውሩ በመግባት በርካታ ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኘው ወልቂጤ ከተማ ተጨማሪ ተጫዋች ወደ ስብስቡ አካቷል፡፡ አማካዩ ተመስገን በጅሮንድ የክለቡ አዲሱ ፈራሚ ሆኗል፡፡

ከዚህ ቀደም በሺንሺቾ ከተማ ፣ ደደቢት እና ኢኮስኮ የመጫወት ዕድል የነበረው አማካዩ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት በሲዳማ ቡና ቤት ግልጋሎት በመስጠት ካሳለፈ በኋላ ወደ ወልቂጤ ከተማ አምርቷል፡፡