መቻል የግብ ዘብ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል

በትናንትናው ዕለት ግርማ ዲሳሳን ያስፈረመው መቻል በሦስት ዓመት ውል ግብ ጠባቂ የግሉ ማድረጉ ታውቋል።

24 ቀናት ባስቆጠረው የዝውውር መስኮት የነቃ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው መቻል እስካሁን ተስፋዬ አለባቸው፣ ከነዓን ማርክነህ፣ ፍፁም ዓለሙ፣ ሳሙኤል ሳሊሶ፣ ዳግም ተፈራ፣ ቶማስ ስምረቱ፣ በረከት ደስታ፣ ግርማ ዲሳሳ እና ምንይሉ ወንድሙን ያስፈረመ ሲሆን አሁን ደግሞ ተስፈኛውን ግብ ጠባቂ ውብሸት ጭላሎ የግሉ አድርጓል።

ከአዳማ ተስፋ ቡድን የተገኘው የግብ ዘቡ ገላን ከተማን ተቀላቅሎ በከፍተኛ ሊጉ የተጫወተ ሲሆን በግማሽ ዓመት ደግሞ በውሰት አዳማ ከተማን ተቀላቅሎ ነበር። በውሰት ወደ አዳማ ያመጡት አሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝም ዳግም በመቻል ስብስባቸው አካተውት የሦስት ዓመት ውል አስፈርመውታል።