የዋልያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ተራዝሟል

ለአይቮሪኮስቱ የአፍሪካ ዋንጫ የሚደረጉ የምድብ ቀሪ አራት የማጣሪያ ጨዋታዎች መገፋታቸው ይፋ ሆኗል።

በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት በቀጣዩ ዓመት እንዲከናወን ቀጠሮ የተያዘለት የአፍሪካ ዋንጫ በሀገሪቱ በሰኔ እና ሀምሌ የክረምት ወቅት መሆኑን ተከትሎ ለወራት መራዘሙ ከሳምንታት በፊት ተገልጿል እንደነበር አይዘነጋም። በዚህም ከሰኔ 15 2015 እስከ ሀምሌ 16 2015 እንዲደረግ ቀጠሮ የተያዘለት ትልቁ የሀገራት ውድድር ወደ ጥር 2016 ተገፍቷል። ከሰዓታት በፊት በወጣ መረጃ ደግሞ የማጣሪያ ጨዋታዎቹም በተመሳሳይ መገፋታቸው ይፋ ሆኗል።

በዚህም የምድብ 3 እና 4 ጨዋታዎች ከመጋቢት 11 እስከ 19፣ የምድብ 5ኛ ጨዋታ ከሰኔ 5 እስከ 13 እንዲሁም የምድብ 6ኛ ጨዋታ ደግሞ ከነሐሴ 29 እስከ መስከረም 1 ድረስ እንዲደረጉ አዲስ መርሐ-ግብር ተይዞላቸዋል።