የጦና ንቦቹ አጥቂ አስፈርመዋል

የአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያሙ ወላይታ ድቻ ሦስተኛ ፈራሚውን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

ከአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ጋር ለመቀጠል ውል ካሰረ በኋላ ሳሙኤል ተስፋዬ እና በኃይሉ ተሻገርን አዲስ ፈራሚዎቹ አድርጎ የከረመው ወላይታ ድቻ የአጥቂው ፍቃዱ መኮንን ዝውውርን አጠናቋል።

ከአንደኛ ሊጉ እስከ ከፍተኛ ሊጉ ከጋሞ ጨንቻ ቆይታ በማድረግ የክለብ ህይወቱን የጀመረው ይህ አጥቂ ስፍራ ተጫዋች 2010 ወደ ሌላኛው ጎረቤት ክለብ አርባምንጭ ከተማ በማምራት ቡድኑ በከፍተኛ ሊጉ መልካም ውጤትን አስመዝግቦ ወደ ሊጉ ማደግ ይችል ዘንድ ጎሎችን በማስቆጠር አስተዋጽኦው የጎላ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ከክለቡ ጋር በፕሪምየር ሊጉ የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ካሳለፈ በኋላ ወደ ወላይታ ድቻ በሁለት ዓመት ውል ተጉዟል፡፡