የመሐመድኑር ናስር ማረፊያ ታውቋል

በበርካታ ክለቦች ሲፈለግ የነበረው አጥቂ በመጨረሻም መዳረሻው ታውቋል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በጅማ አባ ጅፋር ያሳለፈው መሐመድኑር ናስር ከክለቡ ጋር ቀሪ የአንድ ዓመት ውል ቢቀረውም በክረምቱ የዝውውር መስኮት ስሙ ከበርካታ ክለቦች ጋር ሲያያዝ ሰንብቷል። በተለይ ኢትዮጵያ ቡና፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ መቻል እና ፋሲል ከነማ በተጫዋቹ ላይ ጠንካራ ፍላጎታቸውን ቢያሳዩም በመጨረሻም ወደ ቡናማዎቹ ማምራቱን ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።

ከኢትዮጵያ መድን ወጣት ቡድን ተገኝቶ ዋናውን ቡድን በከፍተኛ ሊጉ ያገለገለው ወጣቱ አጥቂ ዓምናም ውሉን በ500 ሺ ብር አፍርሶ ወደ ጅማ አባ ጅፋር አቅንቶ የነበረ ሲሆን ዘንድሮም በስምምነት ከጅማ ጋር ያለውን ቀሪ የአንድ ዓመት ውል አፍርሶ መልቀቂያውን በመቀበል ከደቂቃዎች በፊት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ተገኝቶ ፊርማውን ለቡናማዎቹ አኑሯል።