ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | አርባምንጭ ከተማ የአሰልጣኙን ውል አድሷል

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ያጠናቀቀው አርባምንጭ ከተማ የአሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ እና ረዳቶቹን ውል አራዝሟል፡፡

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ከሌሎች ዓመታት በተሻለ ተፎካካሪነቱ ዐይሎ የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በደረጃ ሰንጠረዡ አምስተኛ ላይ ተቀምጦ ያገባደደው አርባምንጭ ከተማ የዋና አሰልጣኙ ዮሴፍ ገብረወልድን ኮንትራት ለተጨማሪ አንድ ዓመት አድሷል፡፡ የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ አሰልጣኝ በተጠናቀቀው የ2014 የውድድር ዘመን ቡድኑን ጠንካራ በማድረጉ የጥቅማ ጥቅም ማሻሻያ ተደርጎለት ውሉ እንደ ተራዘመ ክለቡ የላከልን መረጃ ያመላክታል፡፡

ቡድኑ ከዋና አሰልጣኙ በተጨማሪ የረዳቶቹ አዱኛ ገላና እና አንተነህ መሳን ውል በተመሳሳይ አድሷል፡፡ ክለቡ በቅርቡም ለቀጣዩ የውድድር ዘመን የአዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ይፈፅማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡