ቅዱስ ጊዮርጊስ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ያደርጋል

ባሳለፍነው ቀን ከታንዛንያው ሲምባ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ያደረጉት ፈረሰኞቹ ሁለተኛ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ሊያደርጉ ነው።

ከዚህ ቀደም በነበረው ዘገባችን የሱዳኑ ክለብ አል ሜሪክ የሜዳ ላይ ጨዋታውን ከሀገር ውጪ ለማከናወን ግዴታ ውስጥ በመግባቱ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም መስከረም 7 ለመጫወት ቀጠሮ መያዙን እና የዝግጅቱን ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ በማድረግ ከአንድ የሀገራችን ክለብ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ለማድረግ ማሰቡን ገልፀን ነበር።

በዚህም መሠረት በአሁኑ ሰዓት ቢሾፍቱ ላይ ልምምዱን እየሰራ የሚገኘው ሜሪክ ማክሰኞ በዘጠኝ ሰዓት ከወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ከሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በቢሸፍቱ የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ጨዋታቸውን ለማድረግ ቀጠሮ መያዛቸውን አውቀናል። ምን አልባት ጨዋታው ሰዓት ቅያሪ የሚደረግ ከሆነ በቀጣይ የምናሳውቅ ይሆናል።