የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታን እንዲመሩ ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ጥሪ ቀረበላቸው

አራት የሀገራችን ኢንተርናሽናል ዳኞች የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታን ሩዋንዳን ላይ ይመራሉ፡፡

የአፍሪካ እግር ኳስ የበላይ አካል የሆነው ካፍ የቀጣይ ዓመት አህጉራዊ የማጣሪያ ውድድሮችን ከያዘው ወር መጨረሻ ጀምሮ ማከናወን ይጀምራል፡፡ ካፍ ከሚያዘጋጃቸው ውድድሮች መካከል አንዱ የሆነው የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች አንዱ ሲሆን መስከረም 8 በሩዋንዳው ሁዬ ስታዲየም አሶሴሽን ስፖርቲቭ ኪጋሊ (ሩዋንዳ) ከ ቴሌኮም ክለብ (ጅቡቲው) ጋር የሚደርጉትን ጨዋታ አራት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች እንዲመሩ መመረጣቸውን ሶከር ኢትዮጵያ መረጃ አግኝታለች፡፡

በዚህም ኃይለየሱስ ባዘዘው በመሀል፣ ትግል ግዛው እና ሸዋንግዛው ተባበል በረዳት እንዲሁም ለሚ ንጉሴ በአራተኛ ዳኝነት ተመድበዋል፡፡ የጨዋታ ታዛቢ በመሆን ደግሞ የማላዊ ዜግነት ያላቸው ራፋዬል ለይሰን ተካተዋል፡፡