ሲዳማ ቡና ከተከላካዩ ጋር ተለያይቷል

የመሀል ተከላካዩ ምንተስኖት ከበደ ከሲዳማ ቡና ጋር በስምምነት ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እየቀረው ተለያይቷል፡፡

በያዝነው ዓመት ከሲዳማ ቡና ጋር ቀሪ የአንድ ዓመት ውል በመኖሩ የቅድመ ውድድር ዝግጅትን በሀዋሳ ከተማ ከክለቡ ጋር ሲሰራ የነበረው የመሀል ተከላካዩ ምንተስኖት ከበደ በጋራ ስምምነት ከክለቡ ጋር ተለያይቷል፡፡ የቀድሞው የመከላከያ ፣ መቀለ 70 እንደርታ እና ኢትዮጵያ ቡና የመሀል ተከላካይ የተጠናቀቀውን የ2014 የውድድር ዘመን ቡናማዎቹን ከለቀቀ በኋላ በሲዳማ ቡና ቤት ለመቆየት የሁለት ዓመት ውልን ማስቀመጡ ይታወሳል፡፡

ከክለቡ ጋር በዘንድሮው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ላይ የሚያስቀጥለው አንድ ዓመት ተጫዋቹ ቢኖረውም ከክለቡ ጋር ባደረገው የጋራ ስምምነት በዛሬው ዕለት መለያየቱ ዕርግጥ ሆኗል፡፡