የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ ውድድሮች የሚደረጉባቸው ከተሞች ታውቀዋል

የ2015 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ የመጀመሪያው ዙር ውድድሮች የሚደረጉባቸው ሁለት ከተሞች ተለይተዋል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የበላይነት በየዓመቱ ከሚዘጋጁ ውድድሮች መካከል የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እንዲሁም ደግሞ የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ውድድር ይጠቀሳሉ፡፡ የ2015 የውድድር ዘመን የሁለቱም ውድድሮች የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ጥቅምት 26 በጁፒተር ሆቴል ከተደረገ በኋላ ውድድሮቹ ኅዳር 10 በይፋ እንደሚጀመሩ መገለፁ አይዘነጋም፡፡

አሁን እንዳገኘነው መረጃ ከሆነ ደግሞ ውድድሮቹ የሚደረጉበት ከተሞች ስለመለየታቸው አረጋግጠናል፡፡ በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ በሀዋሳ ከተማ አርቴፊሻል ስታዲየም ላይ ሲደረግ የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ደግሞ በሰበታ ከተማ በሚገኘው ስታዲየም ላይ የመጀመሪያው ዙር ውድድሮች እንዲደረጉ መወሰኑን ሰምተናል፡፡