የአሠልጣኞች አስተያየት | ኢትዮጵያ መድን 0-0 ሀዋሳ ከተማ

👉”ሦስት ነጥብ ይገባን ነበር ፤ ነገርግን አለመሸነፍም አንድ ትልቅ ነገር ነው” ገብረመድህን ኃይሌ

👉”ጥሩ ፉክክር የታየበት ጨዋታ ነው ፤ ጨዋታው አቻ ይገባዋል” ዘርዓይ ሙሉ

ገብረመድህን ኃይሌ – ኢትዮጵያ መድን

ስለጨዋታው…

ጨዋታው ጥሩ ነው። ከውጤት ጋር ተያይዞ ሦስት ነጥብ ይገባን ነበር ፤ ነገርግን አለመሸነፍም አንድ ትልቅ ነገር ነው። ይህ ቢሆንም ብዙ ኳሶች ስተናል። በአጠቃላይ ግን ተስፋ ሰጪ ነገሮች ነበሩ።

የተገኙ ዕድሎችን ስላለመጠቀማቸው…

የልምድ ጉዳይ ነው። መጓጓት የሚፈጥረው ነገር አለ። ይህ ካልሆነ በስተቀር ተጫዋቾቹ ለመስራት የሚያደርጉት ነገር ጥሩ ነው።

በተከታታይ ስለጣሏቸው ነጥቦች…

የባለፈውን ጨዋታ ተሸንፈናል። በተወሰነ መልኩ ያልተመቸን ነገር አለ። ሜዳው አልተመቸንም። ተጫዋቾቹ በቴክኒክ ረገድ በስለው እንዲጫወቱ ነው ጥረት እያደረግን ያለነው። ከዚህ አንፃር ምቹ የሆነ ሁኔታ አልተፈጠረላቸውም።

ዘርዓይ ሙሉ – ሀዋሳ ከተማ


ስለ ጨዋታው…

ጨዋታው ጥሩ ነበር ማለት ይቻላል ፤ ጥሩ ፉክክር የታየበት ነው። ከሽንፈትም ስለመጣን በብዛት ጎላችንን ጠብቀን ለመጫወት ነበር። እነሱም በተደጋጋሚ አግኝተዋል ማለት ይቻላል። ዛሬ ግብጠባቂያችን ብዙ ኳሶችን አስቀርቷል ማለት ይቻላል። በሙንታሪ ቢያንስ ጎሎች እንዳይገቡ አድርገናል። እኛም በተቃራኒ ኳሶች አግኝተናል። በተለይ በተጀመረ 10 ደቂቃ ሳይሞላ ያገኘነው በተለይ ዓሊ ሱሌይማን ያንን ኳስ ቢጠቀመው ኖሮ ነገሮች ሁሉ በጣም ይቀልሉ ነበር። እንቅስቃሴው መጥፎ አይደለም። ምክንያቱም አንዳንዴ ከሽንፈት ስትመጣ የግድ ነው ወደ አሸናፊነት ለመምጣት ጎልህን ጠብቀህ ነው መሄድ ያለብህና እሱን ለማድረግ ነው የሞከርነው። ዛሬ ኳስ አንሸራሽረን መጫወታችን ደግሞ ከየትኛውም ጊዜ የተሻለ ነው። ትልቁ ነገር ቡድኔ ላይ ያየሁት እሱ ነው። ተከላካዩም አማካዩም ኳሱን ይዘው ነበር ሲጫወቱ የነበረው። የእነሱም ጠንካራ ቡድን ነበር ማለት ይቻላል። ኳሱን በመጫወቱም ጎል ጋር በመድረሱም ወደ መስመር በሚያወጡት ኳስ ለመጠቀም ያስባሉ። ያንን ነው ለመዝጋት ያሰብነውና እንቅስቃሴው በጣም ጥሩ ነው። ትክክለኛ አቻ ነው ማለት ይቻላል። ዛሬ ባደረግነው እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጪ ነገር ቡድናችን ላይ አይተናል።

ስለነበረው የተጫዋቾች እና የአደራደር ቅርፅ ለውጥ…

አንደኛ ከሽንፈት ነው የመጣነው። ቢያንስ ጎሎች ሳይቆጠሩ በሁለት ፈጣን አጥቂዎችን ለመጠቀም ሞክረናል። ከዛ ውጪ ተቃራኒ ቡድን የሚጫወተው በብዛት አንድ ሁለት ከነካኩ በኋላ ወደ ዳር ነው ኳሱ የሚወጣው እና ከዳር የሚሄዱ ኳሶች ጠንካራ ስለሆኑ ሁለተኛ ምርጫችን ደግሞ እነዛን እንቅስቃሴዎች ማቆም ነው። ከዛ ውጪ እኛም ባሰብነው እነሱም ባሰቡት መንገድ ጎል ጋር ደርሰናል ብዬ አስባለሁ። ጥሩ ፉክክር የታየበት ጨዋታ ነው። ጨዋታው አቻ ይገባዋል።