የዐፄዎቹ አሠልጣኝ ቡድናቸውን ዛሬ አይመሩም

ከደቂቃዎች በኋላ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር የ7ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ፋሲል ከነማዎች ዋና አሠልጣኛቸው ጎንደር ይገኛሉ።

የ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ባለቤቱ ፋሲል ከነማ ዘንድሮ በሊጉ እያደረገ ያለው ጉዞ ጥሩ የሚባል እንዳልሆነ ይታወቃል። ቡድኑ በ12 የሊጉ ጨዋታዎች 16 ነጥቦችን በመያዝ የደረጃ ሰንጠረዡ አካፋይ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከደቂቃዎች በኋላም የ7ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ-ግብሩን ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ይከውናል። ድረ-ገፃችን የጨዋታው ጅማሮ መቃረቢያ ላይ በደረሳት መረጃ ዋና አሠልጣኙ ኃይሉ ነጋሽ በአሁኑ ሰዓት ከቡድኑ ጋር እንደማይገኙ ያመላክታል።

አሠልጣኝ ኃይሉ በክለቡ አመራሮች ጥሪ በትናንትናው ዕለት ወደ ጎንደር ያመሩ ሲሆን ዛሬ ረፋድም ከበላይ አካላት ጋር ውይይት እንዳደረጉ ለማወቅ ችለናል። በዚህ ውይይት አሠልጣኙ በስምምነት እንዲለያዩ የተጠየቀ ሲሆን በቅርቡም ድርድሮች ተጠናቀው አሠልጣኙ በይፋ ከክለቡ ጋር በስምምነት እንዲለያዩ እንደሚደረግ አውቀናል።

10 ሰዓት ላይ የሚደረገውን ጨዋታም ምክትል አሠልጣኙ ሙሉቀን አቦሆይ እንደሚመሩት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።