ቻን | ሁለት ተጫዋቾች ብሔራዊ ቡድኑን አልተቀላቀሉም

ዋልያዎቹ የቻን ዝግጅቱን ከደቂቃዎች በፊት ሲጀምር ሁለት ተጫዋቾች በልምምድ መርሐ-ግብሩ አልተሳተፉም።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአልጄሪያ አስተናጋጅነት በሚከናወነው 7ኛው የቻን ውድድር ላይ እንደሚሳተፍ ይታወቃል። ለዚህ ውድድር ዝግጅቱን በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ የጀመረው ብሔራዊ ቡድኑም ከጠራቸው 28 ተጫዋቾች ሁለቱን አለማግኘቱ በስፍራው ተገኝተን ታዝበናል።

በመጀመሪያው የቡድኑ የልምምድ መርሐ-ግብር ተሳትፎ ያላደረጉት ተጫዋቾች አጥቂው ጌታነህ ከበደ እና አማካዩ ታፈሰ ሠለሞን ናቸው። ሁለቱ ተጫዋቾች ብሔራዊ ቡድኑን ያልተቀላቀሉበትን ምክንያት ማወቅ ባንችልም በአሁኑ የቡድኑ ልምምድ ላይ አልተገኙም። ከሁለቱ ተጫዋቾች ውጪ ግን ሀያ ስድስቱም ተጫዋቾች ልምምዱን እየሰሩ ይገኛሉ።