ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሥራ አስኪያጅ ለውጥ አድርጓል


በሊጉ ደካማ የውድድር ተሳትፎን እያደረገ የሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ አዲስ ሥራ አስኪያጅ ሾሟል።

\"\"

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ዳግም የመሳተፍ ዕድልን ያገኘው እና በውጤት ቀውስ ውስጥ ከደረጃ ግርጌው ፈቀቅ ብሎ የሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሰሞኑ ጊዜያዊ አሰልጣኞቹ ገዛኸኝ ከተማ እና ስምዖን አባይን በዋና እና ረዳት የአሰልጣኝነት ሚና መሾሙ ይታወሳል።

አሀን ደግሞ ክለቡ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ከመቀላቀሉ በፊት ከውጤት መጥፋት ጋር በተገናኘ ሥራ አስኪያጅ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩትን አቶ አሸናፊ እጅጉን በትናንትናው ዕለት ከቦታው አንስቷል። በምትካቸውም በስፖርት ክለቡ ውስጥ እና በድርጅቱ በተለያዩ የሥራ መስኮች ሲሰሩ የነበሩትን አቶ ሲሳይ ለማን አዲሱ ሥራ አስኪያጅ በማድረግ መሾሙን ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፅጿል።

\"\"