ቀጣዮቹ የሴቶች ሊግ አስተናጋጅ ከተሞች ተለይተዋል

የ2015 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር እና ከፍተኛ ሊግ ውድድር የሚደረጉባቸውት ቦታዎች ታውቀዋል።

\"\"

በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን አዘጋጅነት የሚደረገው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በሁለተኛው ዙር የሚደረጉባቸው ከተሞች ተለይተው ታውቀዋል።

በሀዋሳ ከተማ ሲካሄድ የሰነበተው የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀጣይ የሁለተኛ ዙር ጨዋታ በባህር ዳር ከተማ የሚደረግ ሲሆን ሰበታ ከተማ ላይ ሲደረግ የነበረው የሴቶች ከፍተኛ ሊግ የሁለተኛ ዙር ጨዋታ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታን ባስተናገደችው ሀዋሳ ከተማ እንደሚካሄክ ታውቋል። የዝውውርና የውድድር መጀመርያ ቀናትም በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ታውቋል።

\"\"