የከፍተኛ ሊግ ሁለተኛው ዙር የሚጀመርበት ቀን እና ቦታ ታውቋል

በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን አወዳዳሪነት የሚደረገው የ2015 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሁለተኛው ዙር መርሀግብር የት እና መቼ እንደሚጀመር ታውቋል።

በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን አዘጋጅነት በሦስት ምድቦች ተከፍሎ በሦስት የተለያዩ ከተሞች እየተደረገ የአንደኛው ዙር ሊጠናቀቅ ጥቂት ጨዋታዎች ብቻ ይቀሩታል ፣ የፌዴሬሽኑ የውድድር ዳይሬክቶሬት ለክለቦች በላከው ደብዳቤ መሠረት ከሆነ የአንደኛው ዙር ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለተኛው ዙር ጨዋታዎች የሚደረግባቸው ከተሞች ይፋ ተደርገዋል።

\"\"

በዚህም መሠረት በባህርዳር ከተማ ሲደረግ የነበረው የምድብ ሀ ጨዋታ በሆሳዕና ከተማ ፣ በጅማ ከተማ ሲደረግ የነበረው የምድብ ለ ውድድር በሀዋሳ ከተማ እና በሆሳዕና ከተማ ሲደረግ የነበረው የምድብ ሐ ውድድር ደግሞ በባቱ (ዝዋይ) ከተማ እንዲደረግ ለክለቦች በተላከው ደብዳቤ ላይ ተገልጿል።

በተጨማሪም የከፍተኛ ሊጉ የዝውውር ጊዜ ከየካቲት 1 እስከ መጋቢት 1 ድረስ ፣ የሁለተኛው ዙር የሚጀመርበት ቀን ደግሞ መጋቢት 10 እንዲሆን ተወስኗል። በተያያዘ ዜና የአንደኛ ሊግ የሁለተኛው ዙር ውድድር የካቲት 14 የሚጀመር ሲሆን በቡራዩ ፣ ደብረማርቆስ ፣ ወልቂጤ እና ቢሾፍቱ ከተሞች የሚካሄድባቸው ቦታዎች መሆናቸውን ሰምተናል።

\"\"