ቀጣዩን የዋልያዎቹ ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል

ከአንድ ወር በኋላ ሞሮኮ ላይ የሚደረገውን የጊኒ እና ኢትዮጵያ ጨዋታ የሚመሩ አልቢትሮች ተለይተዋል።

\"\"

በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከግብፅ፣ ማላዊ እና ጊኒ ጋር ተደልድሎ የምድብ ጨዋታዎችን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በሁለት ጨዋታዎች ሦስት ነጥብ በማግኘት በግብ ልዩነት ቀዳሚውን ደረጃ ይዞ ተቀምጧል። በቀጣዩ የመጋቢት ወር ደግሞ ከጊኒ ጋር የምድብ ሦስተኛ እና አራተኛ ጨዋታውን ሞሮኮ ካዛብላንካ ላይ ያደርጋል።

\"\"

መጋቢት 15 በሞሮኮ ዋና ከተማ ራባት በሚገኘው ልዑል ሞውሊ አብደላ ኮምፕሌክስ የሚደረገውን ጨዋታ ደግሞ ቤኒናዊ ዳኞች እንደሚመሩት ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል። በዚህም ጨዋታውን በመሐል አልቢትርነት ጂንዶ ልዊስ ሆንግናንድአንዴ የሀገራቸው ልጆች ከሆኑት ረዳቶች ኤሪክ አያማቮ እና ጊብማሲዬንዳን ኮዉቶን እንዲሁም ከአራተኛ ዳኛው አዲሳ ሊጋሊ ጋር በጋራ ይመሩታል። ቡርኪናፋሶዋዊው ያሜንጎ ዴቪድ ደግሞ የጨዋታው ኮሚሽነር ሆነው ተመድበዋል።