ኦሴ ማውሊ ዐፄዎቹን ተቀላቅሏል

በአዲስ አሠልጣኝ እየተመሩ የሚገኙት ፋሲል ከነማዎች ጋናዊውን አጥቂ የግላቸው አድርገዋል።

\"\"

አሠልጣኝ አሸናፊ በቀለን በመሾም ከቻን ውድድር መልስ የጀመረውን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የቀረቡት ፋሲል ከነማዎች በመጀመሪያ ጨዋታቸው ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2ለ1 በመርታት ደረጃቸውን ማሻሻላቸው ይታወቃል። በውድድር አጋማሽ የዝውውር መስኮት ዱላ ሙላቱን ብቻ ያስፈረመው ክለቡም ከደቂቃዎች በፊት ኦሴ ማውሊን የግሉ ማድረጉን ይፋ አድርጓል።

\"\"

በመቐለ 70 እንድርታ የኢትዮጵያን እግርኳስ የተዋወቀው ጋናዊው አጥቂ ከዛም ወደ ፋሲል፣ ሰበታ እና ባህር ዳር አምርቶ የተጫወተ ሲሆን ከቀናት በፊት ውል ያለው ባህር ዳር በዲሲፕሊን ምክንያት ከክለቡ እንዳሰናበተው ገልፆ ነበር። አሁን ደግሞ ተጫዋቹ የቀድሞ ክለቡን ፋሲል ከነማ በአንድ ዓመት ውል መቀላቀሉ ተገልጿል።