ሀድያ ሆሳዕና የቅሬታ ደብዳቤን አስገብቷል

ሀድያ ሆሳዕና በኢትዮጵያ መድን 1ለ0 በተሸነፈበት ጨዋታ ላይ ሁለት ጉዳዮችን በመጥቀስ ደረሰብኝ ያለውን በደል ለአወዳዳሪው አካል በደብዳቤ አስገብቷል።

\"\"

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር የመጨረሻ መርሐ-ግብሮች በመደረግ ላይ ይገኛሉ። በትላንትናው ዕለት ቀን 10 ሰዓት ላይ ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ መድን ተጫውተው ጨዋታው መደበኛው ሰዓት ተጠናቆ በተሰጠው የጭማሪ ደቂቃ (90+5\’) ላይ ተቀይሮ የገባው ያሬድ ዳርዛ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል ኢትዮጵያ መድን አሸንፎ መውጣቱ እና በጨዋታውም የሀድያ ሆሳዕና ተጫዋቾች በዳኛው ላይ የተሰማቸውን ቅሬታ ሲያሰሙ መመልከት ችለን ነበር። አሁን ደግሞ ክለቡ ሁለት ጉዳዮችን በዋናነት በመጥቀስ በጨዋታው በደል ደርሶብኛል በማለት ለአወዳዳሪው አካል ደብዳቤን ስለ ማስገባቱ ክለቡ ለዝግጅት ክፍላችን ጠቁመዋል።

\"\"

ክለቡ በደብዳቤው እንዳለው \”የዕለቱ ዋና ዳኛ አሸብር ሰቦቃ በቡድናችን ላይ አላስፈላጊ የሆኑ ውሳኔዎችን ሲሰጥብን እንዲሁም ተጫዋቾቻችን በመሳደብ ጫና ሲያሳድርብን ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ ከተሰጠው ጭማሪ ደቂቃ ውጪ ውጤት የሚለውጥን ተጨማሪ ደቂቃን አጫውቷል ፤ ይሄም አግባብ አይደለም\” በማለት በቅሬታቸው ገልፀዋል።