ዳዊት እስጢፋኖስ ድሬዳዋን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል

ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ልምምድ እየሰራ የሚገኘው አማካዩ ዳዊት እስጢፋኖስ የቀድሞው ክለቡ ድሬዳዋ ከተማን ለመቀላቀል ተቃርቧል።
\"\"

በአሰልጣኝ ዮርዳኖስ አባይ እየተመራ የውድድር ዘመኑን በወጣ ገባ አቋሙ እየዘለቀ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ ከአዳማ ጀምሮ በሚቀጥለው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የሚታይበትን የመሀል ክፍል ለመድፈን በማሰብ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ቢዘጋም \’ከውል ነፃ የሆኑ ተጫዋቾች ወደ የትኛውም ክለብ ያመራሉ\’ በሚለው ህግ መሠረት የቀድሞው የክለቡን አማካይ ዳዊት እስጢፋኖስኖን ለማስፈረም ስለ መቃረቡ ሶከር ኢትዮጵያ ለማወቅ ችላለች።

በአሁኑ ሰዓት ከድሬዳዋ ጋር ልምምድ በመስራት ላይ የሚገኘው እና በኢትዮጵያ ቡና ፣ መቻል ፣ ድሬዳዋ ከተማ ፣ ፋሲል ከነማ ፣ ሰበታ ከተማ ፣ ጅማ አባ ጅፋር ተጫውቶ ያሳለፈው ይህ አማካይ ዛሬ አልያም በቀጣይ ቀናት ከክለቡ የበላይ ኃላፊዎች ጋር በጥቅማጥቅም ጉዳይ የሚስማማ ከሆነ በይፋ የቀድሞው ክለቡን በድጋሚ የሚቀላቀል ይሆናል።

\"\"