የአሰልጣኞች አስተያየት | መቻል 1-1 ሀዋሳ ከተማ

\”ውጤቱ በቂ ነው ባንልም ጨዋታውን አጥተነው ስለነበር አንድ ነጥብ ማግኘታችን ጥሩ ነው።\” አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ

የመቻል እና የሀዋሳ ከተማ ከተማ 1ለ1 ከተጠናቀቀ በኋላ የሀዋሳው አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ አስተያየት ሳይሰጡ ከሜዳ በመውጣታቸው ከመቻሉ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ጋር ያደረግነውን ቆይታ እንዲህ አዘጋጅተነዋል።

\"\"

ስለ ጨዋታው…

\”ወደ ሜዳ የመጣነው ሦስት ነጥብ ለመውሰድ ነው። ሜዳ ላይም ቡድናችን ጥሩ ተጫውቷል ብዬ አስባለሁ። ብዙ የግብ ዕድሎችን ፈጥረናል ግን እንዳለፉት ሁለት ጨዋታዎች ያገኘናቸው የግብ ዕድሎች ባለመጠቀማችን ሳናሸንፍ ቀርተናል። እንደ ቡድን ግን ለዚያውም በዚህ ሜዳ ጥሩ ተጫውተናል ፤ የተሻለ ቡድን ነበረን። በመጨረሻ ደቂቃ እኔም በጣም ደስ ብሎኛል ፤ እንዲህ ደስታዬን ገልጬ ባላውቅም ዛሬ ግን ተጫዋቾቼ ሜዳ ውስጥ በነበራቸው ልፋት ቢያንስ አንድ ነጥብ ይገባቸው ስለነበር ነው። ውጤቱ በቂ ነው ባንልም ጨዋታውን አጥተነው ስለነበር አንድ ነጥብ ማግኘታችን ጥሩ ነው።\”

በእንቅስቃሴያቸው ልክ የግብ ዕድሎችን አለመጠቀማቸው እየፈጠረባቸው ስለሚገኘው ጫና…

\”ሁሌም ጨዋታው ሲጀመር መጀመሪያ ላይ ያገኘሀቸውን የግብ ዕድሎች ከተጠቀምክ ጨዋታውን ትቆጣጠራለህ ፤ ሌሎችንም የግብ ዕድሎች ትፈጥራለህ። ግቦችን ባመከንን ቁጥር እኛ እየወረድን ተጋጣሚያችን ደግሞ ከፍ እያለ መሄዱ አይቀርም። በመጀመሪያዎቹ 10 ደቂቃዎች ሁለት ንፁህ የግብ ዕድሎችን አግኝተናል። ሳሙኤል ሳሊሶ እና እስራኤል እሸቱ ያልተጠቀሙባቸው። እነሱን ብናስቆጥር ጨዋታውን መቆጣጠር እንችል ነበር ግን የመከላከሉም የማጥቃቱም አደረጃጀታችን ጥሩ ነበር። የሜዳው አስቸጋሪነት እንዳለ ሆኖ ከስህተታችን ደግሞ እንማራለን።\”

\"\"

በመጨረሻ ደቂቃ ስላስቆጠሩት ግብ…

\”በመጨረሻዎቹ 15 ደቂቃዎች ዘጠኝ እና አሥር ሆነው ሳጥን ውስጥ እየተከላከሉ ስለነበር ክፍተቶችን ማግኘት አልቻልንም ነበር። እንደዛም ሆኖ ግን ሁለት ንፁህ የግብ ዕድሎችን አግኝተን ነበር በከነዓን በኩል እና እሱን መጠቀም አልቻልንም። መጨረሻ ላይ ግን እግርኳስ እንደዚህ ስለሆነ ባላሰብከው መንገድ ጎል ታገኛለህ። ምናልባት ግብ ጠባቂው ባለቀ ሰዓት መውጣቱ አግዞናል ብዬ አስባለሁ።\”