የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ይፋ ሆኗል

ዋልያዎቹ በቀጣይ ለሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ጥሪ ተደርጎላቸዋል።

\"\"

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአይቮሪኮስት ለሚከናወነው የ2024 አፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። በምድብ መ ተደልድሎ የሚገኘው ብሔራዊ ቡድኑ ሰኔ 13 ከማላዊ አቻው ጋር አምስተኛ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን ያከናውናል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረትም ይህንን ጨዋታ ለማድረግ አሰልጣኝ ዳንኤል ገብረማሪያም ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል። ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች አዳማ በሚገኘው ካኖፒ ሆቴል የፊታችን ሰኞ ሪፖርት አድርገው ልምምድ እንደሚጀምሩም ተያይዞ ተገልጿል።

ግብ ጠባቂዎች

ሰዒድ ሐብታሙ – አዳማ ከተማ
ባህሩ ነጋሽ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ቢኒያም ገነቱ – ወላይታ ድቻ

ተከላካዮች

ያሬድ ባየህ – ባህር ዳር ከተማ
አስቻለው ታመነ – ፋሲል ከነማ
ሚሊዮን ሰለሞን – አዳማ ከተማ
አማኑኤል ተርፉ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሔኖክ አዱኛ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ረመዳን የሱፍ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ዓለምብርሀን ይግዛው – ፋሲል ከነማ
ፍራኦል መንግሥቱ – ባህር ዳር ከተማ

\"\"

አማካዮች

አማኑኤል ዮሐንስ – ኢትዮጵያ ቡና
አለልኝ አዘነ – ባህር ዳር ከተማ
አበባየሁ ሃጂሶ – ወላይታ ድቻ
ከነዓን ማርክነህ – መቻል
ቢኒያም በላይ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሽመልስ በቀለ – ኤንፒ
ወገኔ ገዛኸኝ – ኢትዮጵያ መድን

አጥቂዎች

ዮሴፍ ታረቀኝ – አዳማ ከተማ
ሐብታሙ ታደሰ – ባህር ዳር ከተማ
ብሩክ ሙሉጌታ – ኢትዮጵያ መድን
ዱሬሳ ሹቢሳ – ባህር ዳር ከተማ
አቤል ማሙሽ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ