ነበልባሎቹ ስብስባቸው ይፋ አደረጉ

የዋልያዎቹ ተጋጣሚ የሆነችው ማላዊ የመጨረሻ ስብስቧን ይፋ አድርጋለች።
\"\"
በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን የሚገጥሙት ማላዊዎች ስብሳቸው ይፋ አድርገዋል። እንደ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በተመሳሳይ በጊዜያዊ አሰልጣኝ እየተመሩ ጨዋታቸውን የሚያካሂዱት ማላዊዎች በአብዛኛው በሀገራቸው ሊግ ውስጥ የሚጫወቱ ተጫዋቾች በማሰባሰብ ዋልያዎቹን ለመግጠም ተዘጋጅተዋል።

በትልቅ ደረጃ የዋና አሰልጣኝነት ልምድ በሌለው የአርባ ዘጠኝ ዓመቱ ፓትሪክ ማቤዲ እየተመሩ ልምምዳቸው በማካሄድ የሰነበቱት ነበልባሎቹ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከመግጠማቸው በፊት በአቋም መለኪያ ጨዋታ ሞዛምቢክን የሚገጥሙ ይሆናል።
\"\"
ኢትዮጵያ እና ማላዊ በታሪካቸው አስራ አንድ ግዜ ተገናኝተዋል ፤ ማላዊዎች ሦስት ጨዋታዎች ሲያሸንፉ ዋልያዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ላይ ድል አድርገዋል ፤ የተቀሩት ስድስት ጨዋታዎች ደግሞ በአቻ ውጤት የተጠናቀቁ ናቸው።

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ዝርዝር 👇

\"\"