ፋሲል ከነማ አዲስ አሠልጣኝ ለመሾም ከስምምነት ደርሷል

የ2013 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ ፋሲል ከነማ ለቀጣይ የውድድር ዓመት አዲስ አሠልጣኝ ሊሾም ነው።

ከከፍተኛ ሊግ አድጎ በ2009 በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በመሳተፍ የጀመረው እና ከአምስት ዓመት የሊጉ ቆይታ በኋላ የሊጉንም ዋንጫ በማንሳት ጠንካራ ክለብ እየገነባ መሆኑን ያስመሰከረው ፋሲል ከነማ በዘንድሮ የውድድር ዓመት ከዚህ ቀደም ከሚታወቁበት ጥንካሬ ተቀዛቅዞ መቅረቡ እየታየ ይገኛል።
\"\"
ወደ ቀድሞ ጥንካሬያቸው የሚመልሳቸውን አሰልጣኝ ፍለጋ ለወራት ሲያጤኑ የቆዮት ፋሲል ከነማዎች ያሳለፍነው ዓርብ ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር አብሮ ለመስራት ከስምምነት መድረሳቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

የስምምነቱ አጠቃላይ ዝርዝር ሁኔታዎች እና ይፋዊ የፊርማ ሥነ ስርዓት በቅርቡ በሚጠራ ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ እንደሚደረግ ሰምተናል።
\"\"
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከዚህ ቀደም በፋሲል ከነማ ቤት ውጤታማ የማሰልጠን ቆይታ እንደነበራቸው ይታወቃል።