የዋልያዎቹን ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል

ነገ 11 ሰዓት የሚደረገውን የኢትዮጵያ እና ማላዊ ጨዋታ ከምዕራብ አፍሪካ የመጡ ዳኞች ይመሩታል።
\"\"
የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታዎች እየተደረጉ የሚገኝ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያም ወደ ውድድሩ ለማለፍ ያላት ዕድል ሙሉ ለሙሉ ቢመክንም የመርሐ-ግብር ማሟያ ጨዋታዎቿን ታደርጋለች። ከቀሯት ሁለት ጨዋታዎች መካከል ደግሞ ነገ በሞዛምቢክ ከማላዊ አቻዋ ጋር ትፋለማለች። ይህንን ጨዋታም ቤኒናዊ ዳኞች እንደሚመሩት ታውቋል።

አመሻሽ 11 ሰዓት ሲል የሚደረገውን ጨዋታ በዋና ዳኝነት ጂንዶ ሆንግናንዳንዴ ሲመሩት ኤሪክ አልሪች እና ናርሲስ ኮቶን በረዳትነት እንዲሁም ታኒስላ ዴጂናንቺ በአራተኛ ዳኝነት የሚሳተፉ ይሆናል። ዩጋንዳዊው ዩሱፍ ሱሌይማን ደግሞ የጨዋታው ኮሚሽነር በመሆን ሞዛምቢክ ደርሰዋል።
\"\"
በሠላሳዎቹ መጨረሻ የዕድሜ ክልል ላይ የሚገኙት ጂንዶ ልዊስ ሆንግናንዳንዴ በዚሁ ምድብ ካዛብላንካ ላይ በመሐመድ 5ኛ ስታዲየም ኢትዮጵያ እና ጊኒ ያደረጉትን ጨዋታ መርተው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ጨዋታውም በጊኒ 2ለ0 አሸናፊነት ተገባዶ እንደነበር አይዘነጋም።