አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከሩዋንዳ ተመልሰዋል

የቀድሞ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በሩዋንዳ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል።
\"\"
ዐፄዎቹን ለማሰልጠን ከስምምነት የደረሱት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በትናትናው ዕለት የተካሄደውን የሩዋንዳ እና የሞዛምፒክ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታን በቦታው በመታደም መከታተላቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች። የጉዛቸው ዋና ዓላማ በቅርቡ ከስምምነት ለደረሱት ፋሲል ከነማ የሚሆኑ ተጫዋቾችን ለመመልመል እና ቡድኑን ለማጠናከር የሚያስችሉ ስራዎችን ለመከወን እንደሆነ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
\"\"
በሩዋንዳ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ዛሬ ወደ አዲስ አበባ የተመለሱት አሰልጣኝ ውበቱ ለሦስት ዓመት ከፋሲል ከነማ ጋር የሚያቆያቸውን ስምምነት የፈፀሙ ሲሆን በቅርቡ የስምምነታቸው ዝርዝር ሁኔታ በጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚገለፅ ይጠበቃል።