የሴቶች ክልል ክለቦች ሻምፒዮና በአምቦ ጎል አሸናፊነት ተጠናቋል

ወደ 2016 የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ የሚያድጉ ሁለት ክለቦችን ለመለየት በዘጠኝ ክለቦች መካከል ከሰኔ 14 ጀምሮ በሀዋሳ ከተማ ሲደረግ የነበረው የኢትዮጵያ ሴቶች ክልል ክለቦች ሻምፒዮና በዛሬው ዕለት የኦሮሚያ ተወካዩን አምቦ ጎል ፕሮጀክት የዋንጫ አሸናፊ በማድረግ ተጠናቋል።
\"\"\"\"

አስቀድሞ ቀትር ላይ ሦስተኛ ደረጃን ለመያዝ በሲዳማ ፓይለት እና በጉለሌ ክፍለ ከተማ መካከል የተደረገው የደረጃ ጨዋታ ሲዳማ ፓይለት 2ለ1 አሸንፎ ደረጃውን መቆናጠጥ ችሏል።

\"\"

በመቀጠል በአምቦ ጎል ፕሮጀክት እና በደብረማርቆስ ከተማ መካከል የፍፃሜ መርሀግብር 9 ሰዓት ሲል ጀምሯል። ይህንን ጨዋታ በክብር እንግድነት በመገኘት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባሉ አቶ አዲሱ ቃሚሶ እና የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌድሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ አንበሴ አበበን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ይህንን ጨዋታ ያስጀመሩ ሲሆን በውጤቱም አምቦ ጎል ፕሮጀክት 5ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፈው የውድድሩ አሸናፊ በመሆን አጠናቀዋል።

\"\"

ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ከአንድ እስከ ሦስት ለወጡት ክለቦች የሜዳልያ ሽልማትን ጨምሮ የውድድሩ አሸናፊ አምቦ ጎል የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት የተበረከተለት ሲሆን በቀጣዩ ዓመት አምቦ ጎል እና ደብረማርቆስ ከተማ በኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ላይ ተሳታፊ ይሆናል።
\"\"