ሦስቱ የትግራይ ክልል ክለቦች መግለጫ አወጡ

መቐለ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎና ስሑል ሽረ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወሰነው ውሳኔ ተቃወሙ።

በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ላለፉት ሦስት የውድድር ዓመታት ከውድድር ርቀው የቆዩት የትግራይ ክልል ክለቦች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከቀናት በፊት የወሰነው ውሳኔ በመቃወም ለባለድርሻ አካላት ደብዳቤ ልከዋል።
\"\"
በነበረው አስገዳጅ ሁኔታ ምክንያት ላለፉት ዓመታት ከውድድር ለመራቅ እንደተገደዱ የገለፁት ወልዋሎዎች ስፖርት ለማህበራዊ ትስስር እና ሰላም ያለው የላቀ ሚና በመገንዘብ ጉዳዩ ከስራ አስፈፃሚ ባሻገር ጠቅላላ ጉባኤውም ሊመክርበት እንደሚገባ ጠቅሰዋል። ክለቡ ጨምሮም የሊግ ካምፓኒው እንዲመሰረት የነበራቸው ወሳኝ ተሳትፎ በመገንዘብና ክለቡ ከውድድር የወጣበት ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ካምፓኒው ክለቡን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለመመለስ በሚደረገው ጥረት የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቋል።

\"\"

በሰኔ አምስት ቀን ያላቸውን ቅሬታ በደብዳቤ ያሳወቁት ስሑል ሽረዎችም ፌዴሬሽኑ ውሳኔው ይፋዊ በሆነ መንገድ ለክለቡ አለማሳወቁ ቅሬታ እንዳደረባቸው ገልፀዋል። ጨምረውም ከውድድር የራቁበት ምክንያት በአቅም ማነስ ሳይሆን በክልሉ በነበረው ጦርነት መሆኑ በመግለፅ ጉዳዩ በተጠቀሰው መተዳደሪያ ደንብ መታየት አይገባውም ነበር ብለዋል። ክለቡ ከዚህ በተጨማሪም በክልሉ ላለፉት ሁለት ዓመታት ኮሚኒኬሽን እና መንገድ መዘጋቱ እየታወቀ ክለቦቹ በውድድር አልነበራችሁም በሚል ይህንን ውሳኔ መስጠት ተገቢ አለመሆኑ ገልፀዋል።
\"\"\"\"

መቐለ 70 እንደርታዎች በበኩላቸው ከውሳኔው በኋላ ዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍና ሀገር አቀፍ ደንቦች እና ልምዶች መሰረት አድርገው ሰፊ ውይይት እንዳደረጉ ገልፀው ፌዴሬሽኑ አንድ እርከን ወርዳቹ ተጫወቱ የሚለው ውሳኔ ለመወሰን ያስችሉታል ያልዋቸውን ነጥቦች በመጥቀስ ክለባቸው በጦርነቱ ወቅቱ የተጫዋቾቹና ሰራተኞቹን ህይወት ለመታደግ እና ቋሚና ተንቀሳቃሽ ሀብቱ ማዳል ያልቻለበት አስቸጋሪ ጊዜያትን እንዳሳለፈ ጠቅሰዋል። ክለቡ ጨምሮም ፌዴሬሽኑ የክለቡን ሁኔታ ለማወቅ ያሳየው እንቅስቃሴ ዘገምተኛ መሆኑ በመግለፅ የተወሰነው ውሳኔ በድጋሜ እንዲታይ እና የተፈጠሩት ግድፈቶች በማረም የደረሰበትን ጉዳት በሚክስ መልኩ ፍትሃዊ ውሳኔ እንዲሰጠው በደብዳቤ ጠይቋል።

\"\"

\"\"