የጣና ሞገዶቹ የመጀመሪያ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል

ፍሬው ሰለሞን ባህርዳር ከተማን በይፋ ተቀላቅሏል።
\"\"

በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ማጣሪያ የሚሳተፈው ባህር ዳር ከተማ ለሚቀጥለው የውድድር ዘመን ይረዳው ዘንድ ዝውውሮችን እያደረገ ሲገኝ በዛሬው ዕለትም የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።
\"\"

የቀድሞው ሀላባ ከተማ ፣ ሙገር ሲሚንቶ፣ ሃዋሳ ከተማ ፣ ወልቂጤ ከተማ ፣ መቻል  እና የሲዳማ ቡና ተጫዋች የነበረው ፍሬው ሰለሞን የጣና ሞገዶቹን መቀላቀሉን ክለቡ ይፋ አድርጓል።