ፋሲል ከነማ የመጀመሪያ ተጫዋቹን አስፈረመ

ውበቱ አባተን ዳግም አሰልጣኛቸው ያደረጉት አፄዎቹ የመስመር አጥቂውን የመጀመሪያ ፈራሚ አድርገዋል።

\"\"
አሰልጣኝ ውበቱ አባተን ከሦስት የውድድር ዓመታት በኋላ በድጋሚ አሰልጣኙ አድርጎ መቅጠሩን ከሳምንታት በፊት ያስነበብናችሁ ፋሲል ከነማዎች በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት የመጀመሪያ ፈራሚያቸውን  በእጃቸው አስገብተዋል። የመስመር አጥቂው ቃልኪዳን ዘላለም ደግሞ ክለቡን በይፋ የተቀላቀለው ተጫዋች ሆኗል።

\"\"
ከኢትዮጵያ ቡና ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ ክለቡን በፕሪምየር ሊጉ በማገልገል የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው ቃልኪዳን በመቀጠል በደደቢት እና ሰበታ ከተማ እንዲሁም ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናትን ደግሞ በወላይታ ድቻ ካሳለፈ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው የጎንደሩ ክለብ መሆኑ ተሰምቷል። ተጫዋቹም ለክለቡ የሁለት ዓመት የውል ኮንትራትም ተፈራርሟል።

በቀድሞ አሠልጣኙ ክስ እግድ የተላለፈበት ክለቡ ተጫዋች እንዳያስፈርም በመታገዱ ተጫዋቹ በፌዴሬሽን ፊት ውሉ እንዳልፀደቀ ታውቋል።