ኢትዮጵያ መድን ወደ ዝውውሩ ገብቷል

በአሠልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚመራው ኢትዮጵያ መድን የመጀመሪያ ተጫዋች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።
\"\"
በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተመልሶ 3ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኢትዮጵያ መድን ከቀናት በፊት በተከፈተው የዝውውር መስኮት መሳተፍ ጀምሯል። በዚህም የአማካይ መስመር ተጫዋቹን ሙሴ ከቤላን ማስፈረሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
\"\"
ከኢትዮጵያ ቡና ተስፋ ቡድን የተገኘው ሙሴ ወደ ጅማ አባጅፋር እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በኢትዮ ኤሌክትሪክ ያሳለፈ ሲሆን አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ መድን የእግርኳስ ህይወቱን ለመቀጠል ፊርማ ማኖሩ ታውቋል።