ቸርነት ጉግሳ የጣና ሞገዱን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለተከታታይ ሁለት ዓመታት የሊጉን ዋንጫ ያነሳው የመስመር አጥው ቸርነት ጉግሳ ባህርዳር ከተማን ለመቀላቀል በዛሬው ዕለት ተስማምቷል።
\"\"
የ2015 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ሁለተኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ የፈፀሙት ባህርዳር ከተማዎች ዛሬ ወደ ዝውውሩ ጎራ በማለት ፍሬው ሰለሞንን ያስፈረሙ ሲሆን አሁን ደግሞ ቸርነት ጉግሳን የግላቸው ለማድረግ በእጅጉ መቃረባቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።

ከወላይታ ድቻ ወጣት ቡድን እስከ ዋናው ማገልገል ከቻ በኋላ ከአምስት ዓመታት የክለቡ ቆይታ መልስ በቅዱስ ጊዮርጊስ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በመጫወት ከክለቡ ጋር የሊጉን ዋንጫ ለተከታታይ ዓመት ያሳካው የመስመር ተጫዋቹ ከፈረሰኞቹ ጋር ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ የተሻለ ክፍያ ያቀረቡለትን ባህርዳር ከተማዎችን በሁለት ዓመት ውል ለመቀላቀል ዛሬ ስምምነት ፈፅሟል።
\"\"
ተጫዋቹ ከጊዮርጊስ ቀሪ የአንድ ወር ውል ያለው ሲሆን አዲስ ነገር እስካልተፈጠረ ድረስ ከውል ማብቂያው በኋላ በይፋ የሚፀድቅ ይሆናል።