ንግድ ባንክ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል

የአሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገዱ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የግራ መስመር ተከላካይ እና አጥቂ አስፈረመ።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ በቀጣዩ የውድድር ዘመን ለመሳተፍ ኪቲካ ጀማ እና እንዳለ ዮሐንስን አስፈርሞ የነበረው የአሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገዱ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከባህርዳር ከተማ ጋር ቀሪ ውል እያለው በስምምነት የተለያየውን የግራ መስመር ተከላካዩ ተስፋዬ ታምራት እና በተጠናቀቀው ዓመት በድሬዳዋ ከተማ ግልጋሎት የሰጠውን ቢኒያም ጌታቸው አስፈርሟል።
\"\"
የቀድሞው የኢኮስኮ ፣ ገላን እና ኢትዮጵያ መድን ተጫዋች ከባህርዳር ከተማ ጋር የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ካሳለፈ በኋላ ቀሪ አንድ ዓመት እያለው በስምምነት ተለያይቶ ማረፊያውን በገላን እና መድን ያሰለጠኑትን የቀድሞው አሰልጣኙን ቡድን ንግን ባንክ ዛሬ በሁለት ዓመት ተቀላቅሏል።
\"\"
ከሀምበሪቾ ዱራሜ የተገኘው የቀድሞው የአክሱም ከተማ ፣ ስልጤ ወራቤ እና አዲስአበባ ከተማ አጥቂ የነበረው ቢኒያም የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ወደ ድሬዳዋ አምርቶ የአንድ ዓመት ቆይታን ያደረገ ሲሆን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግንም በከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ዝርዝር ውስጥ ራሱን በማስፈር በ14 ግቦች ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ማጠናቀቁ ይታወሳል። ከምስራቁ ክለቡ ጋር ውሉን ያጠናቀቀው አጥቂው የንግድ ባንክ አራተኛ ፈራሚ ሆኖ በሁለት ዓመት ውል የክለቡ አዲሱ ፈራሚ ሆኗል።