ዐፄዎቹ ሁለተኛ ተጫዋች ለማግኘት ተቃርበዋል

ከቀናት በፊት ቃልኪዳን ዘላለምን ያስፈረሙት ፋሲል ከነማዎች ሁለተኛ ተጫዋች ወደ ስብስባቸው ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሰዋል።
\"\"
አሠልጣኝ ውበቱ አባተን የሾመው ፋሲል ከነማ ምንም እንኳን በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፊት ተጫዋች በይፋ እንዳያስፈርም እግድ ቢጣልበትም በዝውውሩ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ እየቀላቀለ ይገኛል። ከቀናት በፊት እንዳስነበብነው በወላይታ ድቻ ቤት ያለፉትን ሁለት ዓመታት ግልጋሎት የሰጠውን አጥቂ ቃልኪዳን ዘላለምን ያስፈረሙ ሲሆን አሁን ደግሞ ፊታቸውን ወደ ተከላካይ መስመር በማዞር አዲስ ተጫዋች ወደ ቡድናቸው ለማካተት እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኙ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።
\"\"
ቡድኑን ለመቀላቀል ከጫፍ የደረሰው ተጫዋች እዮብ ማቲዮስ ነው። ከአዳማ ተስፋ ቡድን የተገኘው ተጫዋቹ ያለፉትን ሦስት የውድድር ዓመታት በዋናው ቡድን የተጫወተ ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ በተሻለ ደረጃ የመጫወቻ ደቂቃ አግኝቶ ግልጋሎት ሲሰጥ ነበር። በመሐል እና በግራ መስመር ተከላካይነት የሚጫወተው እዮብ በቀጣዩ ዓመት ቀይ እና ነጭ መለያን ለመልበስ ከክለቡ ጋር በብዙ ጉዳዮች መስማማት ላይ እንደደረሰ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።