የጣና ሞገዶቹ የግብ ዘብ አስፈርመዋል

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ኢትዮጵያን የሚወክለው ባህር ዳር ከተማ ግብ ጠባቂ አስፈርሟል።
\"\"
በቅዱስ ጊዮርጊስ ተበልጦ የሊጉን ዋንጫ ማንሳት ያልቻለው ባህር ዳር ከተማ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ኢትዮጵያን እንደሚወክል ይታወቃል። ለዚህ ውድድር እና ለቀጣዩ ዓመት የሊጉ ጨዋታዎች ራሱን እያጠናከረ የሚገኝ ሲሆን ከቀናት በፊትም ፍሬው ሠለሞንን ማስፈረሙ ይታወቃል። አሁን ደግሞ በግብ ብረቶቹ መሐል የሚቆመውን አላዛር ማርቆስ በሁለት ዓመት ውል ማስፈረሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
\"\"
በሀዋሳ ከተማ ተስፋ ቡድን የተገኘው ተጫዋቹ 2013 ላይ ወደ ዋናው ቡድን አድጎ ግልጋሎት የሰጠ ሲሆን ወደ ጅማ አባ ጅፋርም አቅንቶ ተጫውቶ እንደነበር አይዘነጋም። ተጫዋቹ በአሠልጣኝ ተመስገን ዳና ተጠርቶ በሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ የውድድሩ ምርጥ በረኛ ተብሎም ነበር።