ኢትዮጵያ መድን አማካይ አስፈርሟል

በዝውውሩ በንቃት እየተሳተፈ የሚገኘው ኢትዮጵያ መድን የተከላካይ አማካይ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።
\"\"
በአሠልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚመራው ኢትዮጵያ መድን በቀጣይ የውድድር ዓመት ተጠናክሮ ለመቅረብ ከወዲሁ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን እስካሁንም ሦስት ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ መቀላቀሉን አስነብበን ነበር። ድረ-ገፃችን አሁን በደረሳት መረጃ መሠረት ደግሞ ቡድኑ 4ኛ ፈራሚውን አግኝቷል።

ኢትዮጵያ መድንን የተቀላቀለው ተጫዋች ንጋቱ ገብረስላሴ ነው። የተከላካይ አማካዩ ከዚህ ቀደም በጅማ አባ ጅፋር የሊጉን ዋንጫ ያነሳ ሲሆን እስከ 2013 በቡድኑ ግልጋሎት ከሰጠ በኋላም ወደ ወላይታ ድቻ አምርቶ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ተጫውቶ ነበር። አሁን ደግሞ በመድን ቤት በጋራ ሻምፒዮን ከሆኑት የቀድሞ አሠልጣኙ ገብረመድህን ጋር ለመስራት ዝውውሩን አከናውኗል።
\"\"
አሁንም ኢትዮጵያ መድን ተጫዋቾችን በፌዴሬሽን ፊት ማስፈረም ስለማይችል የተጫዋቹ ውል እንዳልፀደቀ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።