ወላይታ የቀድሞው ተጫዋቹን አስፈረመ

የአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹው ወላይታ ድቻ የቀድሞው ተጫዋቹን አስፈርሟል።
\"\"
ዘግየት ብሎም ቢሆን ወደ ተጫዋቾች የዝውውር መስኮት የተቀላቀለው ወላይታ ድቻ ከባዬ ገዛኸኝ እና አብነት ደምሴ በመቀጠል ሦስተኛውን አዲሱ ፈራሚ የመስመር አጥቂው ፀጋዬ ብርሀኑን በሁለት ዓመት ውል አስፈርሞታል።
\"\"
ከወላይታ ድቻ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ ለዋናው ቡድን ለአምስት ተከታታይ ዓመታት ግልጋሎት ከሰጠ በኋላ በ2014 የውድድር ዘመን ሀድያ ሆሳዕናን በመቀላቀል ያለፉትን ሁለት ዓመታት በክለቡ ካሳለፈ በኋላ ወደ ቀድሞው የልጅነት ክለቡ የተመለሰበትን ዝውውር አገባዷል።

እስካሁን ያስፈረማቸው ሦስቱም አዳዲስ ተጫዋቾች የቀድሞ ተጫዋቾቹ የሆኑት ድቻ አሁንም በዝውውሩ ተሳትፎ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።