ሲዳማ ቡና አጥቂ አስፈርሟል

በትናንትናው ዕለት ወደ ዝውውሩ በመግባት አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረም የጀመረው ሲዳማ ቡና አራተኛ ተጫዋች አግኝቷል።
\"\"
በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሁለት አሠልጣኞች ተመርቶ የነበረው ሲዳማ ቡና በቀጣዩ የውድድር ዓመት ከአሠልጣኝ ሥዩም ከበደ ጋር ለመቀጠል ከወሰነ ከቀናት በኋላ በዝውውሩ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል። እስካሁንም ፍቅረየሱስ ተ/ብርሃን፣ ብርሃኑ በቀለ እንዲሁም ደስታ ዮሐንስን ያስፈረመ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ፊቱን ወደ አጥቂ መስመር ተጫዋች በማዞር አብዱራህማን ሙባረክን የግሉ አድርጓል።
\"\"
የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና፣ ፋሲል ከነማ፣ ወልቂጤ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ተጫዋች ዘንድሮ የመጀመሪያውን ዙር ያለክለብ አሳልፎ የነበረ ሲሆን በሁለተኛው ዙር ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በማምራት መልካም የሚባል ጊዜን በግሉ ማሳለፉ አይዘነጋም። አሁን ደግሞ በሲዳማ ቤት ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ግልጋሎት ለመስጠት ፊርማውን አኑሯል።