ሀድያ ሆሳዕና አንድ ተጫዋች ሲያስፈርም የነባር ተጫዋች ውልም አድሷል

የአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌው ሀድያ ሆሳዕና የቀድሞው ተጫዋቹን ሲያስፈርም የተከላካዩንም ውል አራዝሟል።
\"\"
በአዲሱ አሰልጣኛቸው ዮሐንስ ሳህሌ መሪነት ቀጣዩን የውድድር ዓመት የሚጀምሩት ሀድያ ሆሳዕናዎች ከደቂቃዎች በፊት ግብ ጠባቂው ምሕረትአብ ገብረህይወትን ያስፈረሙ ሲሆን ከአጥቂው ዳዋ ሆቴሳ ጋር ስምምነት መፈፀማቸውን ጠቁመናችሁ ነበር። አሁን ደግሞ ክለቡ የቀድሞው ተጫዋቹን ሲያስፈርም የተከላካያቸውን ውልም ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል።
\"\"
በረከት ወልደዮሐንስ ወደ ቀድሞው ክለቡ የሚመልሰውን ዝውውር አጠናቋል። በሀድያ ሆሳዕና ረዘም ያሉ ዓመታትን ካሳለፈ በኋላ ያለፉትን አንድ ዓመት ከግማሽ ወራት በወላይታ ድቻ ቆይታ የነበረው የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ በድጋሜ ወደ ቀድሞው ክለቡ ተመልሷል።

ቡድኑ የዳግም ንጉሴን ውልም ለተጨማሪ ዓመት አድሷል። የቀድሞው የሲዳማ ቡና እና ወልቂጤ ከተማ ተጫዋች የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ባሳለፈበት ክለብ ተጨማሪ አንድ ዓመት ለማገልገል ውሉን አራዝሟል።