ነብሮቹ አንድ ተጫዋቾች አስፈርመዋል

ሀድያ ሆሳዕናዎች ግብ ጠባቂ አስፈርመዋል።

ዮሐንስ ሳህሌን ዋና አሰልጣኝ አድርገው የሾሙት ሀድያ ሆሳዕናዎች ባለፈው የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ጥሩ እንቅስቃሴ ያደረገው ተጫዋቾች የግላቸው አድርገዋል።
\"\"
በዛሬው ዕለት ነብሮቹን ለመቀላቀል ስምምነት የፈፀመው ግብ ጠባቂው ምሕረትአብ ገብረህይወት ሲሆን ባለፈው የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ስልጤ ወራቤ ከዛ በፊትም ለደደቢት እና መቐለ 70 እንደርታ መጫወት ችሏል። በአሰልጣኝ ዮሐንስ ስርም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን፣ በመከላከያ እና መቐለ 70 እንደርታ ተጫውቶ አሳልፏል።
\"\"
በትናንትናው ዕለት ዳዋ ሆቴሳን ለማስፈርም ከስምምነት የደረሱት ነብሮቹ በቀጣይ ቀናት የአጥቂ ዝውውርን ጨምሮ የነባር ተጫዋቾች ውል እንደሚያድሱ ይጠበቃል።