ሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ተጫዋቹን አስፈርሟል

በትላንትናው ዕለት የስድስት ተጫዋቾችን ውል ያደሰው ሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ አዲስ ፈራሚውን በዛሬው ዕለት ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።
\"\"
ለ2016 የውድድር ዘመን የአሰልጣኝ ዘርዐይ ሙሉን ውል ያራዘሙት እና በትላንትናው ዕለት የስድስት ነባር ተጫዋቾቹን ውል ለተጨማሪ ዓመት ያራዘሙት ሀዋሳ ከተማዎች የመጀመሪያ የክለቡ አዲሱ ፈራሚያቸው የመስመር ተከላካዩ እንየው ካሳሁን መሆኑን ክለቡ በተለይ ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቋል።
\"\"
የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እና ፋሲል ከነማ የቀኝ መስመር ተከላካይ ያለፉትን ሦስት የውድድር ዓመታት በምስራቁ ክለብ ድሬዳዋ ከተማ ካሳለፈ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው በሁለት ዓመት ውል ሀዋሳ ከተማ ሆኗል።